Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በዚ​ያም ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶች፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም የሰ​ለለ ብዙ ድው​ያን ተኝ​ተው የው​ኃ​ዉን መና​ወጥ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በእነዚህም መመላለሻዎች ውስጥ ብዙ አካለ ስንኩላን፣ ዐይነ ስውሮች፣ ዐንካሶችና ሽባዎች ይተኙ ነበር። [የውሃውንም መንቀሳቀስ እየተጠባበቁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በእነዚህም ውስጥ ብዙ ድኩማን፥ ዐይነ ሥውሮች፥ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሰዎች ይተኙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 [በጣም ብዙ በሽተኞች፥ ዕውሮች አንካሶችና ሽባዎች በመተላለፊያዎቹ ተኝተው ነበር። እነዚህ የውሃውን መንቀሳቀስ ይጠባበቁ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 5:3
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሄዳ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንና የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን ለዮ​ሐ​ንስ ንገ​ሩት፤ ዕው​ሮች ያያሉ፤ አን​ካ​ሶ​ችም ይሄ​ዳሉ፤ ለም​ጻ​ሞ​ችም ይነ​ጻሉ፤ ደን​ቆ​ሮ​ችም ይሰ​ማሉ፤ ሙታ​ንም ይነ​ሣሉ፤ ለድ​ሆ​ችም ወን​ጌል ይሰ​በ​ካል።


ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ድዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ በኢየሱስም እግር አጠገብ አስቀመጡአቸው፤ ፈወሳቸውም፤


መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፣ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽማ ትጨልማለች።


ለም​ት​ሻ​ውና ለም​ት​ታ​ገሥ፥ ዝም ብላም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን ተስፋ ለም​ታ​ደ​ርግ ነፍስ መል​ካም ነው።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።


የማ​ይ​ታ​የ​ውን ተስፋ ብና​ደ​ርግ ግን እር​ሱን ተስፋ አድ​ር​ገን በእ​ርሱ እንደ ጸናን መጠን ትዕ​ግ​ሥ​ታ​ችን ይታ​ወ​ቃል።


የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፥ መንገዴን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፥ ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አነሣ። ከዚ​ህም በኋላ በእ​ርሱ ላይ የዘ​ረ​ጋት እጁ ደረ​ቀች፤ ወደ እር​ሱም ይመ​ል​ሳት ዘንድ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ ወርዶ ውኃ​ዉን በሚ​ያ​ና​ው​ጠው ጊዜ፥ ከው​ኃዉ መና​ወጥ በኋላ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወርዶ የሚ​ጠ​መቅ ካለ​በት ደዌ ሁሉ ይፈ​ወስ ነበ​ርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች