Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከአ​ይ​ሁ​ድም ይህ​ቺን ጽሕ​ፈት ያነ​በ​ብ​ዋት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን የሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ለከ​ተማ ቅርብ ነበ​ርና፤ ጽሕ​ፈ​ቱም የተ​ጻ​ፈው በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ፥ በሮ​ማ​ይ​ስ​ጥና በግ​ሪክ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ከከተማው አጠገብ ስለ ነበር ብዙዎቹ አይሁድ ጽሑፉን አነበቡት፤ ጽሑፉም፣ በአራማይክና በላቲን፣ በግሪክም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ስለ ነበር፥ ከአይሁድ ብዙዎቹ ጽሑፉን አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፥ በላቲንና በግሪክ ቋንቋ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 19:20
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በራ​ስ​ጌ​ውም ደብ​ዳቤ ጻፉ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በሮ​ማ​ይ​ስጥ፥ በጽ​ር​ዕና በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ሆኖ “የአ​ይ​ሁድ ንጉ​ሣ​ቸው ይህ ነው” የሚል ነበር።


ጲላ​ጦ​ስም ይህን ሰምቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ውጭ አወ​ጣው፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ገበታ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው “ጸፍ​ጸፍ” በሚ​ሉት ቦታ ላይ በወ​ን​በር ተቀ​መጠ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።


ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው።


በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።


በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ራ​ቸው በሰ​ሙም ጊዜ ጸጥ ብለው አዳ​መ​ጡት።


ሁላ​ች​ንም በም​ድር ላይ በወ​ደ​ቅን ጊዜ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፦ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ? በሾለ ብረት ላይ መር​ገጥ ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል’ የሚ​ለ​ኝን ቃል ሰማሁ።


ስለ​ዚ​ህም ኢየ​ሱስ ሕዝ​ቡን በደሙ ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ ከከ​ተማ ውጭ ተሰ​ቀለ።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው፤ እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች