የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ቱም ለአ​ሳ​ላ​ፊ​ዎቹ፥ “የሚ​ላ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ርጉ” አለ​ቻ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናቱም በዚያ የነበሩትን አገልጋዮች፣ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናቱም ለአገልጋዮቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፤” አለቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ እናቱ እዚያ ለነበሩት አገልጋዮች፦ “እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” አለቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 2:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲሁ አደ​ረገ።


እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም አደ​ረ​ግሁ፤ ቀን ለቀ​ንም እክ​ቴን እንደ ስደ​ተኛ እክት አወ​ጣሁ፤ በማ​ታም ጊዜ ግን​ቡን በእጄ ነደ​ልሁ፤ በጨ​ለ​ማም አወ​ጣ​ሁት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም በት​ከ​ሻዬ ላይ አን​ግቼ ተሸ​ከ​ም​ሁት።


ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።


እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።


እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው።


አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።


ከተ​ፈ​ጸ​መም በኋላ ለሚ​ታ​ዘ​ዝ​ለት ሁሉ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኅን ሆነ።


ከወ​ይ​ንም ከሚ​ወ​ጣው ሁሉ አት​ብላ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጣ፤ ርኩ​ስ​ንም ነገር ሁሉ አት​ብላ፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ትን ሁሉ ጠብቁ” አለው።


ወደ አውድማውም ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች።