የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እራትም ቀርቦ ሳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ የስምዖንን ልጅ የአስቆሮቱን ይሁዳ ልብ አነሣሥቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እራትም ሲበሉ፥ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካስገባ በኋላ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ራት ይበሉ ነበር፤ የስምዖን ልጅ አስቆሮታዊው ይሁዳ ግን ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሐሳብ አሳደረበት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 13:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


በሌ​ሊ​ትም ተነ​ሣሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ር​ገው ዘንድ በልቤ ያኖ​ረ​ውን ለማ​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ሁም፤ ተቀ​ም​ጬ​በት ከነ​በ​ረው እን​ስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እን​ስሳ አል​ነ​በ​ረም።


ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።


ቍጥሩ ከዐ​ሥራ ሁለቱ በነ​በ​ረው በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ይሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ያውቅ ነበ​ርና ስለ​ዚህ “ሁላ​ችሁ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” አለ።


ራት ከሚ​በ​ሉ​በት ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን አኖ​ረና ማበሻ ጨርቅ አን​ሥቶ ወገ​ቡን ታጠቀ።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ሐና​ንያ ሆይ፥ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ታታ​ል​ለው ዘንድ፥ የመ​ሬ​ት​ህ​ንም ዋጋ ከፍ​ለህ ታስ​ቀር ዘንድ ሰይ​ጣን በል​ብህ እን​ዴት አደረ?


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


እኛ ሁላ​ችን ቀድሞ እንደ ሥጋ​ችን ምኞት ኖርን፤ የሥ​ጋ​ች​ን​ንም ፈቃ​ድና ያሰ​ብ​ነ​ውን አደ​ረ​ግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥ​አ​ንም ሁሉ የጥ​ፋት ልጆች ሆንን።


እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።