የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የን​ጉ​ሡና የመ​ኳ​ን​ንቱ ልብ ይጠ​ፋል፤ ካህ​ና​ቱም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ነቢ​ያ​ቱም ያደ​ን​ቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“በዚያ ቀን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ንጉሡና ሹማምቱ ወኔ ይከዳቸዋል፤ ካህናቱ ድንጋጤ ይውጣቸዋል፤ ነቢያቱም ብርክ ይይዛቸዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“በዚያም ቀን፥ ይላል ጌታ፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይሣቀቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ቀን ንጉሡና ባለሟሎቹ ፍርሀት ያድርባቸዋል፤ ካህናት ይንቀጠቀጣሉ፤ ነቢያትም ይደነግጣሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 4:9
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ በሁ​ለት ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ሸሹ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደ​ውም መን​ገድ ሄዱ።


ሕይ​ወ​ት​ህን ከጥ​ፋት የሚ​ያ​ድ​ናት፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በም​ሕ​ረቱ የሚ​ከ​ል​ልህ፥


በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ወ​ር​ድ​ባ​ቸው ፍር​ሀ​ትና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ የተ​ነሣ ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ።


የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ።


ባለ​ፈም ጊዜ ይወ​ስ​ዳ​ች​ኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያል​ፋል፤ በሌ​ሊት ክፉ ተስፋ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ያዘ​ና​ችሁ፥ መስ​ማ​ትን ተማሩ።”


ሌባ በተ​ያዘ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር፤ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ እነ​ር​ሱና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያፍ​ራሉ።


ትታ​ረ​ዱና ትበ​ተኑ ዘንድ ቀና​ችሁ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እንደ ተወ​ደደ የሸ​ክላ ዕቃ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ች​ሁና እና​ንተ እረ​ኞች! አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የበ​ጎች አው​ራ​ዎች! ጩኹ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?


ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁ​ለ​ቱም ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ። ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሄዱ።


‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”