የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምና​ል​ባት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ይሰሙ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ይመ​ለሱ ይሆ​ናል፤ እኔም ስለ ሥራ​ቸው ክፋት ያሰ​ብ​ሁ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር እተ​ዋ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምናልባትም ሰምተው እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስላደረጉት ክፋት ላመጣባቸው ያሰብሁትን ቅጣት እተዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምናልባት ይሰሙ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ላደርግባቸው ያሰብሁትን ክፉ ነገር እተዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምናልባት ሕዝቡ አዳምጠው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ የሚመለሱም ከሆነ ከክፋታቸው ሁሉ የተነሣ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት እተዋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምናልባት ይሰሙ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፥ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 26:3
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ሊገ​ጥ​ሙ​አ​ቸ​ውም ወጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ሁለት ትና​ንሽ የፍ​የል መን​ጋ​ዎች ሆነው በፊ​ታ​ቸው ሰፈሩ፤ ሶር​ያ​ው​ያን ግን ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋት ነበር።


እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።


አሁ​ንም መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን አሳ​ምሩ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ች​ሁን ክፉ ነገር ይተ​ዋል።


በውኑ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና ሕዝቡ ሁሉ ገደ​ሉ​ትን? በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ሩ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ አል​ተ​ማ​ለ​ሉ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የተ​ና​ገ​ረ​ባ​ቸ​ውን ክፉ ነገር አይ​ተ​ዉ​ምን? እኛም በነ​ፍ​ሳ​ችን ላይ ታላቅ ክፋት እና​ደ​ር​ጋ​ለን።”


ምና​ል​ባት የይ​ሁዳ ቤት ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ፥ እኔም በደ​ላ​ቸ​ው​ንና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር እል ዘንድ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ ያል​ሁ​ት​ንና ያሰ​ብ​ሁ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆ​ናል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቍጣ​ውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምና​ል​ባት ልመ​ና​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትደ​ርስ ይሆ​ናል፤ ሁሉም ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸው ይመ​ለሱ ይሆ​ናል።”


አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የስ​ደ​ተኛ እክት አዘ​ጋጅ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ቀን ለቀን ተማ​ረክ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ከስ​ፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ተማ​ር​ከህ ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ምን​አ​ል​ባት ያስ​ተ​ውሉ ይሆ​ናል።


“ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጋት ኀጢ​አት ሁሉ ቢመ​ለስ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ቢጠ​ብቅ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


እኔ አም​ላክ ነኝ እንጂ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና፥ በመ​ካ​ካ​ል​ህም ቅዱሱ ነኝና እን​ግ​ዲህ የቍ​ጣ​ዬን መቅ​ሠ​ፍት አላ​ደ​ር​ግም፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም ያጠ​ፉት ዘንድ አል​ተ​ውም፤ ወደ ከተ​ማም አል​ገ​ባም አልሁ።


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀ​ገሬ ሳለሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ይህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋ​ሽም፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ ከክ​ፉው ነገ​ርም የም​ት​መ​ለስ አም​ላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ወደ ተር​ሴስ ለመ​ኰ​ብ​ለል ፈጥኜ ነበር።