የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተ ሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፤ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 7:1
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ወደ መር​ከ​ብም አንተ ልጆ​ች​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ትገ​ባ​ለህ።


የኖኅ ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ኖኅም በት​ው​ልዱ ጻድቅ፥ ፍጹ​ምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው።


በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ።


ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ።


በእ​ርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆ​ና​ለሁ፤ ከዐ​መ​ፃ​ዬም ራሴን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።


በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።


እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያን ይተዋል።


የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።


እነ​ዚህ ሦስቱ ሰዎች ኖኅና ዳን​ኤል ኢዮ​ብም በመ​ካ​ከ​ልዋ ቢኖሩ በጽ​ድ​ቃ​ቸው የገዛ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድ​ናሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፣ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲሁ ይሆ​ናል።


ተስ​ፋዉ ለእ​ና​ን​ተና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ለሚ​ጠ​ራ​ቸው ርቀው ለነ​በሩ ሁሉ ነውና።”


ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።