Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 17:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲሁ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው ሁሉ፣ በሰው ልጅ ዘመንም እንደዚሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በኖኅ ዘመንም እንደሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመንም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በኖኅ ዘመን እንደሆነው ዐይነት የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜም እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 17:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


መብ​ረቅ ብልጭ ብሎ ከሰ​ማይ ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ እን​ደ​ሚ​ያ​በራ የሰው ልጅ አመ​ጣጡ እን​ዲሁ ነውና።


ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከሰው ልጆች ቀኖች አን​ዲ​ቱን ታዩ ዘንድ የም​ት​መ​ኙ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ነገር ግን አታ​ዩ​አ​ትም።


በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውሃ ሰጥሞ ጠፋ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ክፉ ሥራ በም​ድር ላይ እን​ደ​በዛ፥ የል​ባ​ቸው ዐሳብ ምኞ​ትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እን​ደ​ሆነ አየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ ፈጥኖ ይፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ እም​ነ​ትን ያገኝ ይሆን?”


ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።


እነ​ሆም፥ በዓ​ልን፥ ደስ​ታ​ንና ሐሴ​ትን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም አረ​ዳ​ችሁ፤ “ነገ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ብላ፤ እን​ጠ​ጣም፤” እያ​ላ​ችሁ ሥጋን በላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ጠጣ​ችሁ።


“አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገ​ል​ጋይ ያለው ከእ​ና​ንተ ማን ነው? ከእ​ር​ሻው በተ​መ​ለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥ​ነህ ወደ​ዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማ​ዕድ ተቀ​መጥ ይለ​ዋ​ልን?


ኖኅ ወደ መር​ከብ እስከ ገባ​በት ቀን ድረስ ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ሲያ​ገ​ቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥ​ፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድ​ርጎ አጠፋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች