Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ኖኅና ወንዶች ልጆቹ፣ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለመትረፍ ወደ መርከቧ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ኖኅ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኖኅ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ኖኅም ስለ ጥፋት ውኂ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 7:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኖኅ ወደ መር​ከብ እስከ ገባ​በት ቀን ድረስ ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ሲያ​ገ​ቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥ​ፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድ​ርጎ አጠፋ።


ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና።


ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ወደ መር​ከ​ብም አንተ ልጆ​ች​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ትገ​ባ​ለህ።


ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።


ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች