የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 48:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ህም ነገር በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባ​ታ​ችን ደከመ” ብለው ለዮ​ሴፍ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ምና​ሴ​ንና ኤፍ​ሬ​ምን ይዞ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ “አባትህ ታሟል” ተብሎ ለዮሴፍ ስለ ተነገረው ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚህም ነገር በኍላ እንዲህ ሆነ እነሆ አባትህ ታምሞአል ብለው ለዮሴፍ ነገሩት እርሱም ሁለትን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 48:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው።


ለያ​ዕ​ቆ​ብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥ​ቶ​ል​ሃል” ብለው ነገ​ሩት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተጠ​ነ​ካ​ከረ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተቀ​መጠ።


አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው።


ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ።


ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ።


ኤል​ሳ​ዕም ሞተ፤ ቀበ​ሩ​ትም። ከሞ​ዓ​ብም አደጋ ጣዮች በየ​ዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር።


ኢዮ​ብም ከደ​ዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮ​ብም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆ​ቹ​ንና የልጅ ልጆ​ቹ​ንም እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ አየ።


በሰ​ገ​ነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይ​ነ​ቀል እን​ደ​ሚ​ደ​ርቅ፥


እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።


ያዕ​ቆ​ብም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ የዮ​ሴ​ፍን ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው፤ በበ​ትሩ ጫፍም ሰገደ።


የዮ​ሴፍ ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ሁለት ነገ​ዶች ነበሩ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ከሚ​ሆን ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውና ከእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በቀር በም​ድሩ ውስጥ ድርሻ አል​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም።