Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 47:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ዮሴ​ፍም ማለ​ለት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ል​ጋው ራስ ላይ ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ያዕቆብም፣ “በል ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፤ እስራኤልም በዐልጋው ራስጌ ላይ ሆኖ ጐንበስ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እርሱም፦ “ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፥ እስራኤልም በአልጋው ራስ ላይ ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ያዕቆብም “ይህን እንደምታደርግ በመሐላ ቃል ግባልኝ” አለው። ዮሴፍ ይህንኑ በመሐላ አረጋገጠለት፤ ያዕቆብም በመኝታው ላይ እንዳለ በመስገድ እግዚአብሔርን አመሰገነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እርሱም፦ ማልልኝ አለው። ዮሴፍም ማለለት እስራኤልም በአልጋው ራስ ላይ ሰገደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 47:31
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም በእ​ኔም፥ በል​ጄም፥ በወ​ገ​ኔም፥ ከእ​ኔም ጋር ባለ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማል​ልኝ፤ ነገር ግን በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጥ​ተህ ለአ​ንተ ቸር​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አን​ተም ለእኔ፥ ለተ​ቀ​ም​ጥ​ህ​ባ​ትም ምድር ቸር​ነ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”


አብ​ር​ሃ​ምም፥ “እሺ እኔ እም​ላ​ለሁ” አለ።


አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ውን፥ የቤ​ቱን ሽማ​ግሌ፥ የከ​ብ​ቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦


ሰው​የ​ውም ደስ አለው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገደ።


“እጅ​ህን በእጄ ላይ አድ​ርግ፤ እኔም አብሬ ከም​ኖ​ራ​ቸው ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይ​ስ​ሐቅ ሚስት እን​ዳ​ት​ወ​ስ​ድ​ለት በሰ​ማ​ይና በም​ድር አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ል​ሃ​ለሁ፤


አን​ተም ወደ እኔ ብታ​ልፍ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የና​ኮ​ርም አም​ላክ በእኛ መካ​ከል ይፍ​ረድ።” ያዕ​ቆ​ብም በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ማለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የሞቱ ቀን ቀረበ፤ ልጁን ዮሴ​ፍ​ንም ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ​ህን በጕ​ል​በቴ ላይ አድ​ርግ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም እን​ዳ​ት​ቀ​ብ​ረኝ ምሕ​ረ​ት​ንና እው​ነ​ትን አድ​ር​ግ​ልኝ፤


ዮሴ​ፍም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ አጥ​ን​ቴን ከዚህ አን​ሥ​ታ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማ​ላ​ቸው።


አባቴ ሳይ​ሞት አም​ሎ​ኛል፤ እን​ዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ በቈ​ፈ​ር​ሁት መቃ​ብር በከ​ነ​ዓን ምድር በዚያ ቅበ​ረኝ።’ አሁ​ንም ወጥቼ አባ​ቴን ልቅ​በ​ርና ልመ​ለስ።”


የን​ጉ​ሡም አገ​ል​ጋ​ዮች ገብ​ተው፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም ከስ​ምህ ይልቅ መል​ካም ያድ​ርግ፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከዙ​ፋ​ንህ የበ​ለጠ ያድ​ርግ’ ብለው ጌታ​ቸ​ውን ንጉሡ ዳዊ​ትን መረቁ፤” ንጉ​ሡም በአ​ል​ጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።


ያዕ​ቆ​ብም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ የዮ​ሴ​ፍን ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ባረ​ካ​ቸው፤ በበ​ትሩ ጫፍም ሰገደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች