የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 47:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋራ ሲነጻጸር ዐጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያዕቆብም “በመንከራተት ያሳለፍኳቸው ዘመናት መቶ ሠላሳ ናቸው። እነርሱም የቀድሞ አባቶቼ በመንከራተት ካሳለፉአቸው ዘመናት እጅግ ያነሡና ችግር የበዛባቸው ናቸው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ አባቶቼ በእንግነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 47:9
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሴምም አር​ፋ​ክ​ስ​ድን ከወ​ለደ በኋላ አም​ስት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ፤ ሞተም።


የይ​ስ​ሐ​ቅም ዕድሜ መቶ ሰማ​ንያ ዓመት ሆነ።


ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀ​መጠ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም መላው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ።


ፈር​ዖ​ንም ያዕ​ቆ​ብን፥ “የኖ​ር​ኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው።


ማቱ​ሳ​ላም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።


ዮሴ​ፍም በመቶ ዐሥር ዓመት ዕድ​ሜው ሞተ፤ በሽ​ቱም አሹት፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም በሣ​ጥን ውስጥ አኖ​ሩት።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ስደ​ተ​ኞች እንደ ነበሩ እኛ በፊ​ትህ ስደ​ተ​ኞ​ችና መጻ​ተ​ኞች ነን፤ ዘመ​ና​ች​ንም በም​ድር ላይ እንደ ጥላ ናት፤ አት​ጸ​ና​ምም።


“ከሴት የተ​ወ​ለደ ሟች ሰው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥ የቍጣ መከ​ራ​ንም የተ​ሞላ ነው።


ቍጥር የሌ​ላት ክፋት አግ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና፤ ኀጢ​አ​ቶቼ ተገ​ና​ኙኝ፥ ማየ​ትም ተስ​ኖ​ኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።


አቤቱ፥ ታድ​ነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።


አቤቱ አም​ላኬ፥ ብዙ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አደ​ረ​ግህ፥ አሳ​ብ​ህ​ንም ምንም የሚ​መ​ስ​ለው የለም፤ አወ​ራሁ፥ ተና​ገ​ርሁ፥ ከቍ​ጥ​ርም በዛ።


የነ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳ​ኔን አቆ​ምሁ።


ፈር​ዖ​ን​ንም በተ​ና​ገ​ሩት ጊዜ ሙሴ ሰማ​ንያ ዓመት ሆኖት ነበር፤ አሮ​ንም ሰማ​ንያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ።


እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ እመኑ፥ ጨክ​ኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላ​ች​ሁም እና​ንተ እን​ግ​ዶች እንደ ሆና​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ከሥ​ጋ​ች​ሁም ተለ​ይ​ታ​ችሁ ወደ ጌታ​ችን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።


በዚህ የሚ​ኖር ከተማ ያለን አይ​ደ​ለም፤ የም​ት​መ​ጣ​ውን እን​ሻ​ለን እንጂ።


ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ።


ወዳጆች ሆይ! ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤