የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 26:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ድ​ርም ቀድሞ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን ከሆ​ነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስ​ሐ​ቅም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ፣ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። ይሥሐቅም የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ ወደሚኖርበት ወደ ጌራራ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ፥ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወድ አቢሜሌክ ወደ ግውራራ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 26:1
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።


እን​ዲ​ህም ሆነ፥ አብ​ር​ሃ​ምም ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ባረ​ከው፤ ይስ​ሐ​ቅም ዐዘ​ቅተ ራእይ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው ምንጭ አጠ​ገብ ኖረ።


ያዕ​ቆ​ብም ለዔ​ሳው እን​ጀ​ራና የም​ስር ንፍሮ ሰጠው፤ በላ፥ ጠጣ፥ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ዔሳ​ውም ብኵ​ር​ና​ውን አቃ​ለ​ላት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ህል ሸመታ ከመ​ጡት ጋር ገቡ፤ በከ​ነ​ዓን ሀገር ራብ ነበ​ርና።


ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።


በዳ​ዊ​ትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተ​ከ​ታ​ታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳ​ኦ​ልና በቤቱ ላይ ደም አለ​በት፥”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ሂድ፤ አንተ ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኸው ሕዝ​ብህ ጋር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ወደ ማል​ሁ​ባት ምድር ውጣ።


እንዲህም ሆነ፥ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።