Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 12:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚያም ምድር ጽኑ ራብ ገብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አብራም ለጥቂት ጊዜ በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ወረደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በምድርም ራብ ሆነ፥ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በከነዓን ምድር ራብ ገባ፤ ራብም እየበረታ በመሄዱ አብራም የራቡን ጊዜ ለማሳለፍ በስተደቡብ ርቆ ወደ ግብጽ አገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በምድርም ራብ ሆነ አብራንምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 12:10
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


በግ​ብ​ፅና በከ​ነ​ዓን ሀገር ሁሉ ረኃ​ብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሚ​በ​ሉት አጡ።


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


ስለ ድርቅ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


ፈጥ​ነ​ውም ሥራ​ውን ረሱ፥ በም​ክ​ሩም አል​ጸ​ኑም።


በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም።


በሰ​ማ​ር​ያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነ​ሆም፥ የአ​ህያ ራስ በኀ​ምሳ ብር፥ የድ​ርጎ አንድ አራ​ተኛ የሚ​ሆን ኵስሐ ርግ​ብም በአ​ም​ስት ብር እስ​ኪ​ሽጥ ድረስ ከበ​ቡ​አት።


ኤል​ሳ​ዕም ዳግ​መኛ ወደ ጌል​ጌላ ተመ​ለሰ፤ በም​ድ​ርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች በፊቱ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ኤል​ሳ​ዕም ሎሌ​ውን፥ “ታላ​ቁን ምን​ቸት ጣድ፤ ለነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብ​ስ​ል​ላ​ቸው” አለው።


በዳ​ዊ​ትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተ​ከ​ታ​ታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳ​ኦ​ልና በቤቱ ላይ ደም አለ​በት፥”


እንዲህም ሆነ፥ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።


በም​ድ​ርም ሁሉ እህል አል​ነ​በ​ረም፤ ራብ እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ ከራ​ብም የተ​ነሣ የግ​ብፅ ምድ​ርና የከ​ነ​ዓን ምድር ተጐዳ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ህል ሸመታ ከመ​ጡት ጋር ገቡ፤ በከ​ነ​ዓን ሀገር ራብ ነበ​ርና።


ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።


በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች