የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሎሌ​ውም፥ “ሴቲቱ ምና​ል​ባት ወደ​ዚህ ሀገር ከእኔ ጋር ለመ​ም​ጣት ባት​ወ​ድ​ድስ ልጅ​ህን ወደ መጣ​ህ​በት ሀገር ልመ​ል​ሰ​ውን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዩም፣ “ሴቲቱ ከእኔ ጋራ ወደዚህ ምድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆን ምን አደርጋለሁ? ልጅህን አንተ ወደ መጣህበት አገር ልውሰደውን?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሎሌውም፦ “ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ልመልሰውን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አገልጋዩም “ምናልባት የምመርጥለት ሴት ከእኔ ጋር ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገውን?” ብሎ ጠየቀ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሎሌውም፦ ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ለመልሰውን? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 24:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ዬ​ንም ሴቲቱ ምና​ል​ባት ከእኔ ጋር መም​ጣ​ትን ባት​ፈ​ቅ​ድስ አል​ሁት።


ነገር ግን ወደ ተወ​ለ​ድ​ሁ​በት ወደ ሀገ​ሬና ወደ ተወ​ላ​ጆች ሂድ፤ ለልጄ ለይ​ስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሚስ​ትን አም​ጣ​ለት።”


ርብ​ቃ​ንም ጠር​ተው፥ “ከዚህ ሰው ጋር ትሄ​ጃ​ለ​ሽን?” አሉ​አት። እር​ስ​ዋም፥ “አዎን እሄ​ዳ​ለሁ” አለች።


አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ልጄን ወደ​ዚያ እን​ዳ​ት​መ​ልስ ተጠ​ን​ቀቅ፤


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ሕዝ​ቤን ልት​ለ​ቃ​ቸው እንቢ ብትል፥ ብት​ይ​ዛ​ቸ​ውም፥


ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤ ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።