የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 22:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህ በኋላ አብርሃምም አገልጋዮቹን፥ “አህያውን ይዛችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ተራራ ሄደን እንሰግዳለን፤ ሰግደንም ወደ እናንተ እንመለሳለን” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው፦ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 22:5
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ብላ​ቴ​ኖቹ ተመ​ለሰ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ አብ​ረው ሄዱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተቀ​መጠ።


አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ቦታ​ውን ከሩቅ አየ።


አብ​ር​ሃ​ምም የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ዕን​ጨት አን​ሥቶ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ አሸ​ከ​መው፤ እር​ሱም እሳ​ቱ​ንና ቢላ​ዋ​ዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ።


ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም፥ “ወደ እና​ንተ እስ​ክ​ን​መ​ለስ ድረስ በዚህ ቈዩን፤ ግር​ግር አት​በሉ፤ አሮ​ንና ሆርም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ ነገ​ረ​ተ​ኛም ቢኖር ወደ እነ​ርሱ ይሂድ” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ ሊያ​ስ​ነ​ሣው እን​ደ​ሚ​ችል አም​ኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም ያው የተ​ሰ​ጠው መታ​ሰ​ቢያ ሆነ​ለት።


እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን የሚ​ያ​ህሉ ምስ​ክ​ሮች እንደ ደመና በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉ​ልን እኛ ደግሞ ሸክ​ምን ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ጭን​ቀት ከእኛ አስ​ወ​ግ​ደን፥ በፊ​ታ​ችን ያለ​ውን ሩጫ በት​ዕ​ግ​ሥት እን​ሩጥ።