የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግን ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተ​ባለ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይም ነበ​ረ​ቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአብራም ሚስት ሦራ፣ ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤ እርሷም አጋር የምትባል ግብጻዊት አገልጋይ ነበረቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር፥ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባርያም ነበረቻት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአብራም ሚስት ሣራይ ገና ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል አንዲት ግብጻዊት አገልጋይ ነበረቻት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባሪያም ነበረቻት

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 16:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


ለአ​ብ​ራ​ምም ስለ እር​ስዋ መል​ካም አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ለእ​ርሱ በጎ​ችም፥ በሬ​ዎ​ችም፥ አህ​ዮ​ችም፥ በቅ​ሎ​ዎ​ችም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችም ነበ​ሩት።


አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ከና​ኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ስለ​ዚች አገ​ል​ጋ​ይ​ህና ስለ ሕፃኑ አት​ዘን፤ ሣራም የም​ት​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃ​ልና።


በፋ​ራን ምድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ እና​ቱም ከም​ድረ ግብፅ ሚስት ወሰ​ደ​ች​ለት።


ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።


ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።


ይህም የሁ​ለቱ ሥር​ዐት ምሳሌ ነው፤ አን​ዲቱ ከደ​ብረ ሲና ለባ​ር​ነት ትወ​ል​ዳ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አጋር ናት።


ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር።


ለሐ​ናም ልጅ ስላ​ል​ነ​በ​ራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕል​ቃ​ናም ከዚ​ያ​ች​ኛ​ይቱ ይልቅ ሐናን ይወ​ድድ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግቶ ነበር።