Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለአ​ብ​ራ​ምም ስለ እር​ስዋ መል​ካም አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ለእ​ርሱ በጎ​ችም፥ በሬ​ዎ​ችም፥ አህ​ዮ​ችም፥ በቅ​ሎ​ዎ​ችም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችም ነበ​ሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በርሷም ምክንያት ፈርዖን አብራምን አክብሮ አስተናገደው፤ በጎችና ከብቶች፣ ተባዕትና እንስት አህዮች፣ ወንድና ሴት አገልጋዮች እንዲሁም ግመሎችን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለአብራምም በእርሷ ምክንያት መልካም አደረገለት፥ ለእርሱ በጎችም በሬዎችም አህዮችም ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችም ግመሎችም ነበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በእርስዋ ምክንያት ንጉሡ አብራምን በደኅና ዐይን ተመለከተው፤ በጎች፥ ከብቶች፥ አህዮች፥ ግመሎች፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለአብራምም ስለእርስዋ መልካም አደረገለት ለእርሱ በጎችም በሬዎችም አህዩችም ወዶችን ሴቶች ባሪያዎችም ግመሎችን ነበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 12:16
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሜ​ሌ​ክም አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብርን በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን አመጣ፤ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሰጠው፤ ሚስ​ቱን ሣራ​ንም መለ​ሰ​ለት።


አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛ​ውን ለኢ​ዮብ ባረከ፤ መን​ጋ​ዎ​ቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድ​ስት ሺህም ግመ​ሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬ​ዎች፥ አንድ ሺህም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ።


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም፥ ወን​ዶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም፥ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም አገ​ኘሁ፤ አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው ለመ​ን​ገር ላክሁ።”


ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌታ​ዬን እጅግ ባረ​ከው፤ አገ​ነ​ነ​ውም፤ ላሞ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ወን​ዶች ባሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ግመ​ሎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም ሰጠው።


ነገር ግን ያ ክፉ አገ​ል​ጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይ​መ​ጣም ቢል፥ በጌ​ታው ቤት ያሉ​ት​ንም ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች ሊደ​በ​ድ​ብና ሊያ​ጕ​ላላ ቢጀ​ምር፥ ከሰ​ካ​ራ​ሞ​ችም ጋር ቢበ​ላና ቢጠጣ፥ ቢሰ​ክ​ርም፥


በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቸ​ውም፤ ንብ​ረ​ታ​ቸው ብዙ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚ​ህም ባን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቻ​ቸ​ውም።


የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግን ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተ​ባለ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይም ነበ​ረ​ቻት።


ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ባለ​ጠጋ ሆነ፤ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ ብዙ ከብ​ትም፤ ላሞ​ችም፥ በጎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችና አህ​ዮ​ችም ሆኑ​ለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች