የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ አብራም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም ዐብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ሲወጣ ዕድሜው 75 ዓመት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብራም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ከካራን ወጥቶ ሄደ፤ በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ ሎጥም አብሮት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 12:4
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አራ​ንም ሎጥን ወለደ።


ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


ከአ​ብ​ራም ጋር የሄ​ደው ሎጥ ደግሞ የላ​ምና የበግ መንጋ ድን​ኳ​ኖ​ችም ነበ​ሩት።


አጋር ይስ​ማ​ኤ​ልን በወ​ለ​ደ​ች​ለት ጊዜ አብ​ራም የሰ​ማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሰው ነበረ።


አብ​ራ​ምም በከ​ነ​ዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን አጋ​ርን ወስዳ ለአ​ብ​ራም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠ​ችው።


አብ​ር​ሃ​ምም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዓመ​ታት እነ​ዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አም​ስት ዓመት ኖረ።


ያዕ​ቆ​ብም ከአ​ዘ​ቅተ መሐላ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።


ከዚ​ህም በኋላ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር ወጥቶ በካ​ራን ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እና​ንተ ወደ አላ​ች​ሁ​ባት ወደ​ዚች ሀገር አመ​ጣው።


አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።


ከዚ​ህም በኋላ ታግሦ ተስ​ፋ​ዉን አገኘ።