የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ከሀ​ገ​ርህ፥ ከዘ​መ​ዶ​ች​ህም፥ ከአ​ባ​ት​ህም ቤት ተለ​ይ​ተህ ውጣ፤ እኔ ወደ​ማ​ሳ​ይ​ህም ምድር ሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ከአገርህ ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን ትተህ፥ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤተሰብ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም አብራምን አለው፤ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 12:1
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ይህ​ችን ምድር ትወ​ር​ሳት ዘንድ እን​ድ​ሰ​ጥህ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ቤት ባወ​ጣኝ ጊዜ አል​ኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድ​ር​ጊ​ልኝ፤ በገ​ባ​ን​በት ሀገር ሁሉ ወን​ድሜ ነው በዪ።’ ”


ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገ​ኔም ሂድ፤ ለል​ጄም ከዚያ ሚስ​ትን ውሰ​ድ​ለት።


ነገር ግን ወደ ተወ​ለ​ድ​ሁ​በት ወደ ሀገ​ሬና ወደ ተወ​ላ​ጆች ሂድ፤ ለልጄ ለይ​ስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሚስ​ትን አም​ጣ​ለት።”


ከአ​ባቴ ቤት፥ ከተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ምድር ያወ​ጣኝ፦ ‘ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ’ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝና የማ​ለ​ልኝ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እርሱ መል​አ​ኩን በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ዳል፤ ከዚ​ያም ለልጄ ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ወደ ግብፅ አት​ው​ረድ፤ እኔ በም​ልህ ምድር ተቀ​መጥ።


አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነህ፤ አብ​ራ​ምን መረ​ጥህ፤ ከዑር ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም አወ​ጣ​ኸው፤ ስሙ​ንም አብ​ር​ሃም አል​ኸው፤


አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን በቴ​ማን ያሉ​ትን ጎዛ​ን​ንና ካራ​ንን፥ ራፌ​ስ​ንም የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?


አንተ ከም​ድር ዳርቻ የያ​ዝ​ሁህ፥ ከማ​ዕ​ዘ​ን​ዋም የጠ​ራ​ሁህ ነህና፦ አንተ ባሪ​ያዬ ነህ፤ መር​ጬ​ሃ​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፤ ያል​ሁህ ሆይ፥


ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አብ​ር​ሃም፥ ወደ ወለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ወደ ሳራ ተመ​ል​ከቱ፤ አንድ ብቻ​ውን በሆነ ጊዜ ጠራ​ሁት፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ ወደ​ድ​ሁ​ትም፤ አበ​ዛ​ሁ​ትም።


“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር በአሉ በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች የተ​ቀ​መጡ፦ አብ​ር​ሃም ብቻ​ውን ሳለ ምድ​ሪ​ቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙ​ዎች ነን፤ ምድ​ሪ​ቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች ይላሉ። ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦


እር​ሱም፥ “አል​ሄ​ድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገ​ሬና ወደ ዘመ​ዶች እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤