Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ቤት ባወ​ጣኝ ጊዜ አል​ኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድ​ር​ጊ​ልኝ፤ በገ​ባ​ን​በት ሀገር ሁሉ ወን​ድሜ ነው በዪ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር አዝዞኝ ከአባቴ ቤት ወጥቼ በየአገሩ ስዞር፣ ‘ለእኔ ያለሽን ፍቅር በዚህ ግለጭልኝ፤ በየደረስንበት ስፍራ ሁሉ “እርሱ ወንድሜ ነው” በዪ’ ብያት ነበር።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ ‘በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኍት በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፤ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለእኔ ተናገሪ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 20:13
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ከሀ​ገ​ርህ፥ ከዘ​መ​ዶ​ች​ህም፥ ከአ​ባ​ት​ህም ቤት ተለ​ይ​ተህ ውጣ፤ እኔ ወደ​ማ​ሳ​ይ​ህም ምድር ሂድ።


አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ።


እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች።


እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ስዋ ደግሞ ራስዋ ወን​ድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅን​ነ​ትና በእጄ ንጹ​ሕ​ነት ይህን አደ​ረ​ግ​ሁት።”


ቤተ መቅ​ደ​ስህ ቅዱስ ነው በጽ​ድ​ቅም ድንቅ ነው። በም​ድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስ​ፋ​ቸው የሆ​ንህ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ሆይ ስማን።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ትፈ​ታ​ተ​ኑት ዘንድ እን​ዴት ተባ​በ​ራ​ችሁ? እነሆ፥ ባል​ሽን የቀ​በ​ሩት ሰዎች እግ​ሮች በበር ናቸው፤ አን​ቺ​ንም ይወ​ስ​ዱ​ሻል” አላት።


አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ።


ሳኦ​ልም አለ፥ “እና​ንተ ስለ እኔ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች