የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህ የሆነው በሐሴቦን ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንና በአስታሮት ይገዛ የነበረውን የዐግን ንጉሥ ባሳንን በኤድራይ ድል ካደረገ በኋላ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀምጦ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም የሆነው በሐሴቦን ከተማ ነግሦ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንንና በዐስታሮትና በኤድረዒ ከተሞች ሆኖ ይገዛ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዖግን ድል ካደረገ በኋላ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 1:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ርና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ረዐ​ይ​ትን በአ​ስ​ጣ​ሮት ቃር​ና​ይም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን ሰዎ​ች​ንና ኦሚ​ዎ​ስን በሴዊ ከተማ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤


“መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንና አሕ​ዛ​ብን ዕድል ፈንታ አድ​ር​ገህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን ምድር፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን ምድር ወረሱ።


እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ምድር ሙሴ እን​ዲህ ብሎ ይህን ሕግ ይገ​ልጥ ጀመር፦


“ከቄ​ድ​ሞ​ትም ምድረ በዳ የሰ​ላ​ምን ቃል ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ወደ ሐሴ​ቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እን​ዲህ ብዬ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክሁ፦


“ተመ​ል​ሰ​ንም በባ​ሳን መን​ገድ ወጣን፤ የባ​ሳን ንጉሥ ዐግም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በኤ​ድ​ራ​ይን ሊዋ​ጉን ወጡ።


በሐ​ሴ​ቦ​ንም ንጉሥ በሴ​ዎን እን​ዳ​ደ​ረ​ግን ፈጽሞ አጠ​ፋ​ና​ቸው፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት፥ የሚ​ሸሽ ሳና​ስ​ቀር ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም ፈጽሞ አጠ​ፋ​ና​ቸው።


የእ​ር​ሱ​ንና የባ​ሳ​ንን ንጉሥ፥ የዐ​ግን ምድር፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን የሁ​ለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንን ነገ​ሥ​ታት ምድር ወሰዱ።