Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ሙሴ እን​ዲ​ነ​ግ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በአርባኛው ዓመት፣ በዐሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን እስራኤላውያንን በሚመለከት እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ሙሴ ለእነርሱ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በአርባኛው ዓመት በዓሥራ አንደኛው ወር መጀመሪያ ቀን፥ ሙሴ፥ ጌታ ስለ እነርሱ ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ግብጽን ለቀው ከወጡ በኋላ አርባኛው ዓመት በገባ በዐሥራ አንደኛው ወር መጀመሪያ ቀን ሙሴ ለሕዝቡ ያስረዳቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-4 በአርባኛው ዓመት በአሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ሙሴ፥ በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀምጦ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ፥ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 1:3
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዛት እነ​ዚህ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።


ካህ​ኑም አሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት፥ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሞተ።


ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች