እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያጸናል፤ በሱባዔውም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በቤተ መቅደስም የጥፋት ርኵሰት ይሆናል፤ እስከ ዘመኑም ፍጻሜ የጥፋት መጨረሻ ይሆናል።”