እርሱንም እልፍ አደረገው፤ ሁለተኛውንም ያመጡት ዘንድ አዘዘ፤ አመጡትም፤ “አንተ የይሁዳ ዘር ያይደለህ የከነዓን ዘር ነህ፤ ውበት አሳተህ፤ ክፉ ፈቃድም ልቡናህን ገለበጠው።