የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ምር​ኮን ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቁጥጥሩም ሥር አደረጋቸው፥ ሜተግ አማ የተባለችውንም ከተማ ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጥቂት ዘግየት ብሎም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርጎ በቊጥጥሩ ሥር አደረጋቸው፤ “ሜቴግ አማ” የተባለችውንም ከተማ ከእነርሱ እጅ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፥ አዋረዳቸውም፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሜቴግ አማ የተባለችውን ከተማ ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 8:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።


ኢዮ​አ​ብና አቢ​ሳም አበ​ኔ​ርን አሳ​ደዱ፤ ፀሐ​ይም ጠለ​ቀች፤ እነ​ር​ሱም በገ​ባ​ዖን ምድረ በዳ መን​ገድ በጋይ ፊት ለፊት እስ​ካ​ለው እስከ አማን ኮረ​ብታ ድረስ መጡ።


ከአ​ሕ​ዛብ ጠብ አድ​ነኝ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፤ የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝብ ተገ​ዛ​ልኝ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ።


በሄ​ድ​ህ​በ​ትም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ ከፊ​ትህ አጠ​ፋሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ እን​ዳሉ እንደ ታላ​ላ​ቆቹ ስም ስም​ህን ታላቅ አደ​ረ​ግሁ።


ልቤ ተስፋ በቈ​ረጠ ጊዜ ከም​ድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ በድ​ን​ጋይ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።


እን​ዲሁ ለስ​ምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ ምኞ​ቴን ሁል​ጊዜ ትሰ​ጠኝ ዘንድ።


እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ተጋ​ደሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሡ፤ ጽድ​ቅን አደ​ረጉ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ውን አገኙ፤ የአ​ና​ብ​ስ​ት​ንም አፍ ዘጉ ።


የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ዳግ​መ​ኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስ​ራ​ኤል ድን​በር አል​ወ​ጡም፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ነበ​ረች።