የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ እሄ​ድና እመ​ላ​ለስ ነበር እንጂ በቤት አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁ​ምና፥

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ድንኳንን ማደሪያዬ አድርጌ ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዝሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ ድንኳንን ማደሪያዬ አድርጌ ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዝሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ በመታደግ ካዳንኩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በድንኳን ውስጥ ሆኜ በየስፍራው ስዘዋወር ኖርኩ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት አልተቀመጥሁምና አንተ የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 7:6
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኦር​ዮም ለዳ​ዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦ​ትና እስ​ራ​ኤል፥ ይሁ​ዳም በድ​ን​ኳን ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ጌታዬ ኢዮ​አ​ብና የጌ​ታ​ዬም አገ​ል​ጋ​ዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍ​ረ​ዋል፤ እኔ ልበ​ላና ልጠጣ ወይስ ከሚ​ስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለ​ሁን? በሕ​ይ​ወ​ት​ህና በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ይህን ነገር አላ​ደ​ር​ገ​ውም” አለው።


ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእ​ር​ስ​ዋም ቤት ይሠ​ራ​ልኝ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ።”


“ሙሴን ተና​ግሮ እንደ አዘ​ዘው በአ​ሳ​የው ምሳሌ የሠ​ራት የም​ስ​ክር ድን​ኳን በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ በም​ድረ በዳ ነበ​ረች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ድ​ንህ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጥህ በሰ​ፈ​ርህ ውስጥ ይሄ​ዳ​ልና ስለ​ዚህ ነው​ረኛ ነገር እን​ዳ​ያ​ይ​ብህ፥ ፊቱ​ንም ከአ​ንተ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ ሰፈ​ርህ የተ​ቀ​ደሰ ይሁን።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


“በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦


በዚ​ያም ዘመን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ነበ​ረ​ችና፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቁ፤