የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ አርባ ዓመ​ትም ነገሠ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ አርባ ዓመትም ገዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ አርባ ዓመትም ገዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት በነገሠበት ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በጠቅላላ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ልጅ ነበረ፥ አርባ ዓመትም ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 5:4
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ።


ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ። በኬ​ብ​ሮን ሰባት ዓመት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።


ከኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያ​ንም እንደ አባ​ቶች ቤቶች ትው​ል​ዶች የኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያን አለቃ ኤር​ያስ ነበረ። ዳዊት በነ​ገሠ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት ይፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ነበረ፤ በእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል በገ​ለ​ዓድ ኢያ​ዜር ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ተገኙ፤


ሰባት ዓመት በኬ​ብ​ሮን፥ ሠላሳ ሦስ​ትም ዓመት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ።


እነ​ዚህ ስድ​ስቱ በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በዚ​ያም ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዕድ​ሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮ​ሴፍ ልጅም ይመ​ስ​ላ​ቸው ነበር።