አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ወደ ምዕራብ ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፤ ያን ቀጥተኛ መንገድ ካለፉ በኋላም ወደ ሰፈር መጡ።
2 ሳሙኤል 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ኢያቡስቴ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት፥ በዓረባም መንገድ ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ቤቱ ውስጥ የገቡት ኢያቡስቴ በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ነበር፤ ወግተው ከገደሉትም በኋላ ራሱን ቈርጠው በመውሰድ፣ ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ መንገድ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቤቱ ውስጥ የገቡት ኢያቡስቴ በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ተኝቶ ሳለ ነበር፤ ወግተው ከገደሉትም በኋላ ራሱን ቆርጠው በመውሰድ፥ ሌሊቱን ሁሉ በዓራባ መንገድ ተጓዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከገቡም በኋላ ወደ ኢያቡስቴ መኝታ ክፍል ዘለቁ፤ እርሱም በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ወግተው ገደሉት፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱ፤ ሌሊቱንም ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ በኩል አልፈው ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ እርሱ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፥ ራሱንም ቆርጠው ወሰዱት፥ በዓረባም መንገድ ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ። |
አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ወደ ምዕራብ ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፤ ያን ቀጥተኛ መንገድ ካለፉ በኋላም ወደ ሰፈር መጡ።
ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ሹሞችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ቡሃቃዎችህም፥ ወደ ምድጃዎችህም ይገባሉ፤
ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፤ ገደለውም፤ ራሱንም ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።
አገላብጠውም የጦር መሣሪያዎችን ገፈፉ፤ በዙሪያቸውም ላሉ ለጣዖታቱና ለሕዝቡ የምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ሁሉ ላኩ።