1 ሳሙኤል 31:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አገላብጠውም የጦር መሣሪያዎችን ገፈፉ፤ በዙሪያቸውም ላሉ ለጣዖታቱና ለሕዝቡ የምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ሀገር ሁሉ ላኩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዚያም የሳኦልን ራስ ቈርጠው፣ የጦር መሣሪያውንም ገፍፈው፣ ለቤተ ጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲናገሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ከዚያም የሳኦልን ራስ ቆርጠው፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈው፥ የምሥራቹን በየቤተ ጣዖቶቻቸውና በሕዝባቸው መካከል እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤም ምድር ሁሉ መልክተኞች ላኩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ልብሱንም ገፈው በማስያዝ ለአማልክቶቻቸው መቅደስና ለሕዝባቸው የድሉን ዜና ያበሥሩ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ላኩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ዕቃውን ገፍፈው ለጣዖታቱ መቅደስ ለሕዝቡም የምስራች ይሰጥ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ሁሉ ሰደዱ። ምዕራፉን ተመልከት |