Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወን​ዙም ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ያፈ​ላል፤ ወጥ​ተ​ውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አል​ጋ​ህም፥ ወደ ሹሞ​ች​ህም ቤት፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ፥ ወደ ቡሃ​ቃ​ዎ​ች​ህም፥ ወደ ምድ​ጃ​ዎ​ች​ህም ይገ​ባሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አባይ በጓጕንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ ዐልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሖቃዎችህ ይገባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አስማተኞችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የዐባይ ወንዝ በጓጒንቸሮች የተሞላ ስለሚሆን፥ ከዚያ እየወጡ ወደ ቤተ መንግሥትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህ፥ ወደ መኳንንትህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፥ እንዲሁም ወደ ምድጃህና ወደ ቡኾ ዕቃዎችህ ሳይቀር ይገባሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ባሪያዎችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ምድጆችህም፥ ወደ ቡሃቃዎችህም ይገባሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 8:3
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የን​ጉሡ ልጅ ዮሳ​ቤት ግን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ሰርቃ ወሰ​ደች፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱን በእ​ል​ፍኝ ውስጥ አኖ​ረ​ቻ​ቸው፤ የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ሚስት ዮሳ​ቤት ከጎ​ቶ​ልያ ፊት ሸሸ​ገ​ችው፤ እር​ስ​ዋም አል​ገ​ደ​ለ​ች​ውም።


ፊን​ሐ​ስም ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፥ ቸነ​ፈ​ሩም ተወ።


ቤቶ​ች​ህም የሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ቤቶች፥ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ቤቶች በእ​ርሱ ይሞ​ላሉ፤ አባ​ቶ​ችህ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ህም አባ​ቶች በም​ድር ላይ ከተ​ቀ​መ​ጡ​በት ቀን ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያላ​ዩት ነው።” ሙሴም ተመ​ልሶ ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጣ።


ሕዝ​ቡም ሊጡን ሳይ​ቦካ ተሸ​ከሙ፤ ቡሃ​ቃ​ው​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው ጠቅ​ል​ለው በት​ከ​ሻ​ቸው ተሸ​ከ​ሙት።


ፈር​ዖ​ንም ጠቢ​ባ​ን​ንና መተ​ተ​ኞ​ችን ጠራ፤ የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ ደግሞ አደ​ረጉ።


ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው።


ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገ​ር​ህን ሁሉ በጓ​ጕ​ን​ቸ​ሮች እመ​ታ​ለሁ፤


ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችም በአ​ንተ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ላይ ይወ​ጣሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች