የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለሳ​ኦ​ልም የኢ​ዮ​ሄል ልጅ ሩጻፋ የተ​ባ​ለች ዕቅ​ብት ነበ​ረ​ችው፤ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን፥ “ወደ አባቴ ዕቅ​ብት ለምን ገባህ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦልም የኢዮሄልን ልጅ ሪጽፋን በቁባትነት አስቀምጧት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፣ “ለምንድን ነው ከአባቴ ቁባት ጋራ የተኛኸው?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦልም ሪጽፋን የምትባለውን የአያን ልጅ በዕቁባትነት አስቀምጦአት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፥ “ለምንድን ነው ከአባቴ ዕቁባት ጋር የተኛኸው?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦል የአያ ልጅ የሆነች ሪጽፋ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴ አበኔርን “ለምን ከአባቴ ቁባት ጋር ተገናኘህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሳኦልም የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ የተባለች ቁባት ነበረችው፥ ኢያቡስቴም አበኔርን፦ ወደ አባቴ ቁባት ለምን ገባህ? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 3:7
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌ​ታ​ህ​ንም ቤት ሰጠ​ሁህ፤ የጌ​ታ​ህ​ንም ሚስ​ቶች በብ​ብ​ትህ ጣል​ሁ​ልህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ቤት ሰጠ​ሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበ​ለጠ እጨ​ም​ር​ልህ ነበር።


የሳ​ኦ​ልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴን ወስዶ ከሰ​ፈር ወደ መሃ​ና​ይም አወ​ጣው፤


እር​ሱም፥ “ፊቱን አይ​መ​ል​ስ​ብ​ሽ​ምና፥ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳን ይድ​ር​ልኝ ዘንድ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እን​ድ​ት​ነ​ግ​ሪው እለ​ም​ን​ሻ​ለሁ” አለ።