የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፣ “ይህ የሞተ ውሻ፣ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሻገርና ራሱን ልቍረጠው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፤ “ይህ የሞተ ውሻ፥ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ የጸሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን እንዴት ይራገማል? እኔ ሄጄ ራሱን ልቊረጠው!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጽሩያም ልጅ አቢሳ ንጉሡን፦ ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን ይረግማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 16:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢሳ ግን፥ “ሳሚ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን ሰድ​ቦ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ ሞት የተ​ገ​ባው አይ​ደ​ለ​ምን?” ብሎ መለሰ።


ዳዊ​ትም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! ዛሬ ታስ​ቱኝ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእ​ስ​ራ​ኤል የሚ​ሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገ​ሥሁ አላ​ው​ቅ​ምን?”


ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።


አበ​ኔ​ርም ኢያ​ቡ​ስቴ እን​ዲህ ስላ​ለው እጅግ ተቈጣ፤ አበ​ኔ​ርም እን​ዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአ​ባ​ትህ ለሳ​ኦል ቤት ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዘ​መ​ዶ​ቹም ቸር​ነት አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ለዳ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጠ​ሁ​ህም፤ አን​ተም ዛሬ ከዚ​ህች ሴት ጋር ስለ ሠራ​ሁት ኀጢ​አት ትከ​ስ​ሰ​ኛ​ለህ።


እር​ሱም፥ “የሞተ ውሻ ወደ​ም​መ​ስል ወደ እኔ ትመ​ለ​ከት ዘንድ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ምን​ድን ነኝ?” ብሎ ሰገደ።


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ን​ስም ይህን ባዩ ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ኤል​ያስ እንደ አደ​ረገ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ ያጥ​ፋ​ቸው እን​ድ​ንል ትፈ​ቅ​ዳ​ለ​ህን?” አሉት።


ጳው​ሎ​ስም፥ “ወን​ድ​ሞች፥ ሊቀ ካህ​ናት መሆ​ኑን አላ​ው​ቅም መጽ​ሐፍ ‘በሕ​ዝ​ብህ አለቃ ላይ ክፉ አት​ና​ገር’ ይላ​ልና” አላ​ቸው።


ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


የጥ​ንት ምሳሌ፦ ‘ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ኀጢ​አት ይወ​ጣል’ እን​ደ​ሚል፥ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።