Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 24:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የጥ​ንት ምሳሌ፦ ‘ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ኀጢ​አት ይወ​ጣል’ እን​ደ​ሚል፥ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? አንተስ የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተ ውሻን? ወይስ ቍንጫ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጥንት፥ ‘ክፋት ክፋትን ይወልዳል’ እንደተባለ፤ አሁንም እጄ በአንተ ላይ አትሆንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለመግደል እንደሚጥር ተመልከት! ማንንም እንደሚያሳድድ አስተውል! የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን? ማንን እንደሚያሳድድ ተመልከት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእስራኤል ንጉሥ ማንም ለማሳደድ መጥቶአል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን ታሳድዳለህን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 24:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤”


አበ​ኔ​ርም ኢያ​ቡ​ስቴ እን​ዲህ ስላ​ለው እጅግ ተቈጣ፤ አበ​ኔ​ርም እን​ዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአ​ባ​ትህ ለሳ​ኦል ቤት ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዘ​መ​ዶ​ቹም ቸር​ነት አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ለዳ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጠ​ሁ​ህም፤ አን​ተም ዛሬ ከዚ​ህች ሴት ጋር ስለ ሠራ​ሁት ኀጢ​አት ትከ​ስ​ሰ​ኛ​ለህ።


ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች።


እር​ሱም፥ “የሞተ ውሻ ወደ​ም​መ​ስል ወደ እኔ ትመ​ለ​ከት ዘንድ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ምን​ድን ነኝ?” ብሎ ሰገደ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሀ​ገ​ሩን አለ​ቆች ሁሉ ጠርቶ፥ “ተመ​ል​ከቱ፤ ይህም ሰው ክፉ እን​ዲሻ እዩ፤ ስለ ሚስ​ቶቼ ስለ ወን​ዶች ልጆ​ቼና ሴቶች ልጆቼ ላከ​ብኝ፤ ብሬ​ንና ወር​ቄን ግን አል​ከ​ለ​ከ​ል​ሁ​ትም” አላ​ቸው።


ዐመ​ፅን ለምን ተከ​ላ​ችሁ? ኀጢ​አ​ት​ንስ ለምን አጨ​ዳ​ችሁ፤ የሐ​ሰ​ት​ንም ፍሬ በል​ታ​ች​ኋል፤ በሠ​ረ​ገ​ሎ​ች​ህና በሠ​ራ​ዊ​ትህ ብዛት ታም​ነ​ሃል።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው።


አሁ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ ሰው ቆቅን እን​ደ​ሚሻ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነፍ​ሴን ለመ​ሻት ወጥ​ቶ​አ​ልና ደሜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አይ​ፍ​ሰስ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች