የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉሡ ዳዊ​ትም ወደ በው​ሪም መጣ፤ እነ​ሆም፥ ሳሚ የሚ​ባል የጌራ ልጅ ከሳ​ኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየ​ሄ​ደም ይረ​ግ​መው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፣ ከሳኦል ቤተ ሰብ ነገድ የሆነ አንድ ሰው ብቅ አለ፤ እርሱም የጌራ ልጅ ሳሚ ነው፤ እየተራገመም ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፥ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ወጣ፤ ስሙ ሺምዒ ሲሆን የጌራ ልጅ ነው፤ እየተራገመም ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም በደረሰ ጊዜ ከሳኦል ዘመዶች አንዱ የሆነው የጌራ ልጅ ሺምዒ ሊገናኘው ወጥቶ እየተራገመ ወደ እርሱ ቀረበ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡ ዳዊትም ወደ ብራቂም መጣ፥ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፥ እየሄደም ይረግመው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 16:5
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ሁሉ ደረሱ፤ ደክ​መ​ውም ነበር፤ በዚ​ያም ዐረፉ።


ንጉ​ሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ የነ​በ​ረው ሁሉ ለአ​ንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊ​ትህ ሞገ​ስን ላግኝ” አለ።


ወደ ዳዊ​ትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ድን​ጋይ ይወ​ረ​ውር ነበር፤ በን​ጉ​ሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያ​ላኑ ሁሉ ነበሩ።


አንድ ብላ​ቴ​ናም አይቶ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ነገ​ረው፤ እነ​ርሱ ግን ፈጥ​ነው ሄዱ፤ ወደ ባው​ሪ​ምም ወደ አንድ ሰው ቤት መጡ፤ በግ​ቢ​ውም ውስጥ ጕድ​ጓድ ነበ​ረው፤ ወደ​ዚ​ያም ውስጥ ወረዱ፤


ዓረ​ባ​ዊው አቤ​ዔ​ል​ቦን፥ አል​ሞ​ና​ዊው ኤማ​ሱ​ኖስ፥


ባል​ዋም እያ​ለ​ቀሰ ከእ​ር​ስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራ​ቂም ድረስ ተከ​ተ​ላት። አበ​ኔ​ርም፥ “ሂድ፤ ተመ​ለስ” አለው፤ እር​ሱም ተመ​ለሰ።


የቀ​ስ​ቱን አፎት ከፍቶ ክፉ አደ​ረ​ገ​ብኝ፤ በፊ​ቴም ልጓ​ሙን ሰደደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ ጻድቅ ነው።


ልብሱ ነውና፥ ዕር​ቃ​ኑ​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ን​በት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም ሌላ የለ​ው​ምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤ መሓሪ ነኝና።


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


የሰ​ማይ ዎፍ ቃል​ህን ያወ​ጣ​ዋ​ልና፥ ክንፍ ያለ​ውም ነገ​ር​ህን ያወ​ራ​ዋ​ልና በል​ብህ ዐሳብ እን​ኳን ቢሆን ንጉ​ሥን አት​ሳ​ደብ፥ በመ​ኝታ ቤት​ህም ባለ​ጠ​ጋን አት​ሳ​ደብ።


በዚ​ህም በር​ግጥ ጽኑ ረኃብ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋል፤ በተ​ራ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በአ​ለ​ቆ​ችና በመ​ኳ​ን​ን​ቱም ላይ ክፉ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው።