እርሱም፥ “የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለምን በየቀኑ እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን?” አለው። አምኖንም፥ “የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ” አለው።
2 ሳሙኤል 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮናዳብም አለው፦“ ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህም ሊያይህ ይመጣል፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታበስልልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮናዳብም፣ “እንግዲያው ‘ታምሜአለሁ’ ብለህ ዐልጋ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፣ ‘እኅቴ ትዕማር መጥታ የምበላውን ነገር ብትሰጠኝ ደስ ይለኛል፤ መብሉንም እዚሁ አጠገቤ ሆና እያየሁ አዘጋጅታ በእጇ እንድታጐርሰኝ እባክህ ፍቀድልኝ ብለህ ንገረው፣’ ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናዳብም፥ “እንግዲያው የታመምህ መስለህ አልጋ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፥ ‘እኅቴ ትዕማር መጥታ የምበላውን ነገር ትስጠኝ፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርሷ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናዳብም እንዲህ አለው፤ “ይህ ከሆነ እንግዲህ የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣ፥ ‘እኅቴ ትዕማርን መጥታ እንድታስታምመኝ እባክህ ንገራት፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርስዋ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮናዳብም፦ ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፥ አባትህም ሊያይህ በመጣ ጊዜ፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታዘጋጅልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በል አለው። |
እርሱም፥ “የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለምን በየቀኑ እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን?” አለው። አምኖንም፥ “የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ” አለው።
እንዲሁም አምኖን፥ ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊያየው መጣ፤ አምኖንም ንጉሡን፥ “እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታበስልልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ” አለው።
አኪጦፌልም አቤሴሎምን፥ “ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፤ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈርኸው ይሰማሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል” አለው።
አሁንም እናንተ ከሸንጎው ጋር ወደ ሻለቃው ሂዱና የምትመረምሩትና የምትጠይቁት አስመስላችሁ ጳውሎስን እንዲያመጣው ንገሩት፤ እኛ ግን ወደ እናንተ ከመድረሱ አስቀድሞ ልንገድለው ቈርጠናል።”