ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞ ከአፈቀራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፥ “ተነሥተሽ ሂጂ” አላት።
2 ሳሙኤል 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕማርም፥ “ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ እኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ” አለችው፤ አምኖን ግን ቃልዋን አልሰማትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “ይህ አይሆንም! እኔን አስወጥቶ መስደድ፣ አስቀድመህ ካደረስህብኝ በደል የባሰ መፈጸምህ ነው” አለችው። እርሱ ግን አልተቀበላትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም፥ “ይህ አይሆንም! እኔን አስወጥቶ መስደድ፥ አስቀድመህ ካደረስህብኝ በደል የባሰ መፈጸምህ ነው” አለችው። እርሱ ግን ሊሰማት አልፈቀደም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “አይሆንም! እኔን እንደዚህ አድርገህ ብታባርረኝ አሁን ከፈጸምከው በደል ይልቅ የከፋ ኃጢአት ትፈጽማለህ!” አለችው። አምኖን ግን ሊያዳምጣት አልፈቀደም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ አይሆንም፥ ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ እኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ አለችው፥ እርሱ ግን አልሰማትም። |
ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞ ከአፈቀራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፥ “ተነሥተሽ ሂጂ” አላት።