የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ወደ ቤትህ ሂድ፤ እግ​ር​ህ​ንም ታጠብ” አለው። ኦር​ዮም ከን​ጉሡ ቤት ሲወጣ አንድ የን​ጉሥ መል​እ​ክ​ተኛ ተከ​ተ​ለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዳዊት ኦርዮን፣ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም ማለፊያ ምግብ አስከትሎ ላከለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ዳዊት ኦርዮንን፥ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም የምግብ ስጦታ ላከለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ዳዊት ኦርዮን “እንግዲህ ወደ ቤትህ ሂድና እግርህን ታጠብ” አለው፤ ኦርዮም ከዳዊት ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ዳዊትም ወዲያውኑ የምግብ ስጦታ ላከለት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ኦርዮን፦ ወደ ቤትህ ሂድ፥ እግርህንም ታጠብ አለው። ኦርዮም ከንጉሡ ቤት ሲወጣ ማለፊያ የንጉሥ መብል ተከትሎት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 11:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ውኃ እና​ም​ጣ​ላ​ችሁ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም እን​ጠ​ባ​ችሁ።


አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት።


ስም​ዖ​ን​ንም ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው። እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ሊታ​ጠቡ ውኃ አመ​ጣ​ላ​ቸው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ገፈራ ሰጣ​ቸው።


በፊ​ቱም ከአ​ለው መብል ፈን​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የብ​ን​ያ​ምም ፈንታ ከሁሉ አም​ስት እጅ የሚ​በ​ልጥ ነበረ። እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ደስ አላ​ቸው።


እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?


ምክ​ራ​ቸ​ውን ጥልቅ አድ​ር​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ሰ​ውሩ ወዮ​ላ​ቸው! ሥራ​ቸ​ው​ንም በጨ​ለማ ውስጥ አድ​ር​ገው፥ “ማን ያየ​ናል? ወይስ ማን ያው​ቀ​ናል?” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!


የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ፥ የማ​ይ​ታ​ይም የተ​ሸ​ሸገ የለ​ምና።


ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።