የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞ​ኛ​ልና ደግሞ እስ​ካ​ሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያ​ውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደ​ለኝ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ከዚያም፣ ‘እኔ በሞት ጣር ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም፥ ‘እኔ የሞት ጣር ይዞኛል፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱም ‘ወደ እኔ ቀርበህ ግደለኝ፤ በብርቱ ስለ ቈሰልኩ መሞቴ ነው!’ አለኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ ሰውነቴ ዝሎአልና፥ ደግሞ እስከ አሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያው ናትና በላዬ ቆመህ ግደለኝ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 1:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም ከወ​ደቀ በኋላ አለ​መ​ዳ​ኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደ​ል​ሁት፤ በራ​ሱም ላይ የነ​በ​ረ​ውን ዘውድ፥ በክ​ን​ዱም የነ​በ​ረ​ውን ቢተዋ ወሰ​ድሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ወደ ጌታዬ አመ​ጣ​ሁት።”


እር​ሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፤ እኔም አማ​ሌ​ቃዊ ነኝ ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።


ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ዘ​ብ​ቱ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።


በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።


እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።


ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ወ​ጉ​ኝና እን​ዳ​ይ​ሳ​ለ​ቁ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።