Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እር​ሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፤ እኔም አማ​ሌ​ቃዊ ነኝ ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ?’ ሲል ጠየቀኝ፤ “እኔም ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እርሱም፥ ‘አንተ ማን ነህ?’ ብሎ ጠየቀኝ፤ እኔም ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስኩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ማን እንደ ሆንኩ በጠየቀኝ ጊዜም ዐማሌቃዊ መሆኔን ነገርኩት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፥ እኔም፦ አማሌቃዊ ነኝ ብዬ መለስሁለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “እኔ የመ​ጻ​ተ​ኛው የአ​ማ​ሌ​ቃ​ዊው ልጅ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ወደ ኋላ​ውም ዘወር አለና እኔን አይቶ ጠራኝ፤ እኔም፦ እነ​ሆኝ አልሁ።


እር​ሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞ​ኛ​ልና ደግሞ እስ​ካ​ሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያ​ውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደ​ለኝ አለኝ።


ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤ ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወጥ​ተው በጌ​ሴ​ራ​ው​ያ​ንና በአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ቅጽር ባላ​ቸው በጌ​ላ​ም​ሱ​ርና በአ​ኔ​ቆ​ን​ጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀ​ም​ጠው አገ​ኙ​አ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሴቄ​ላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን በአ​ዜብ በሰ​ቄ​ላ​ቅም ላይ ዘም​ተው ነበር፤ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም መት​ተው በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋት ነበር፥


ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።


ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች