Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔም ከወ​ደቀ በኋላ አለ​መ​ዳ​ኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደ​ል​ሁት፤ በራ​ሱም ላይ የነ​በ​ረ​ውን ዘውድ፥ በክ​ን​ዱም የነ​በ​ረ​ውን ቢተዋ ወሰ​ድሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ወደ ጌታዬ አመ​ጣ​ሁት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “መቼም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፣ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፤ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፥ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና በክንዱ ላይ የነበረውን አንባር ወስጄ፥ እነሆ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔም ከወደቀ በኋላ አለ መዳኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፥ በራሱም ላይ የነበረውን ዘውድ በክንዱም የነበረውን ቢተዋ ወሰድሁ፥ ወደዚህም ወደ ጌታዬ አመጣሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:10
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።


እር​ሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞ​ኛ​ልና ደግሞ እስ​ካ​ሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያ​ውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደ​ለኝ አለኝ።


የን​ጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም የሜ​ል​ኮ​ምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብ​ደ​ቱም አንድ መክ​ሊት ወርቅ ያህል ነበር፤ ክቡር ዕን​ቍም ነበ​ረ​በት፤ ዳዊ​ትም በራሱ ላይ አደ​ረ​ገው። ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።


የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።


የራ​ሳ​ችን አክ​ሊል ወድ​ቆ​አል፤ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ና​ልና ወዮ​ልን!


አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።


እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።


ንጉ​ሡም ዶይ​ቅን፥ “አንተ ዞረህ ካህ​ና​ቱን ግደ​ላ​ቸው” አለው። ሶር​ያ​ዊው ዶይ​ቅም ዞሮ ካህ​ና​ቱን ገደ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የበ​ፍታ ኤፉድ የለ​በ​ሱ​ትን ሦስት መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሰዎ​ችን ገደለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች