የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ስለ ሳኦ​ልና ስለ ልጁ ዮና​ታን ይህን የኀ​ዘን ቅኔ ተቀኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የሐዘን እንጕርጕሮ እየተቀኘ አለቀሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የኀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ልጁም ስለ ዮናታን ይህን የሐዘን ቅኔ ተቀኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ስለ ሳኦልና ሰለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኅዘን ቅኔ ተቀኘ፥

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 1:17
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በአ​ጣድ አው​ድማ የሆ​ነ​ውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግ​ብፅ ልቅሶ እን​ዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ነው።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ለሞ​ቱ​ትና ለተ​ገ​ደ​ሉት ሐው​ልት ትከል፤ ኀያ​ላን እን​ዴት ወደቁ!


ንጉ​ሡም ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሰ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “አበ​ኔር ሰነፍ እን​ደ​ሚ​ሞት ይሞ​ታ​ልን?


ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።


ይኸ​ውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ የአ​ሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ ስለ ግብ​ፅና ስለ ኀይ​ልዋ ሁሉ ያሞ​ሹ​ለ​ታል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።