Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ልጁም ስለ ዮናታን ይህን የሐዘን ቅኔ ተቀኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የሐዘን እንጕርጕሮ እየተቀኘ አለቀሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የኀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዳዊ​ትም ስለ ሳኦ​ልና ስለ ልጁ ዮና​ታን ይህን የኀ​ዘን ቅኔ ተቀኘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዳዊትም ስለ ሳኦልና ሰለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኅዘን ቅኔ ተቀኘ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 1:17
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነቢዩ ኤርምያስም ለንጉሥ ኢዮስያስ የለቅሶ ሙሾ አወጣለት፤ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች አልቃሾች ኢዮስያስን በማስታወስ፥ በሚያለቅሱበት ጊዜ በዚሁ በነቢዩ ኤርምያስ የለቅሶ ሙሾ ማልቀስ በእስራኤል አገር የተለመደ ሆነ፤ ይህም የለቅሶ ሙሾ የእስራኤልን የለቅሶ ሰቆቃ በያዘ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።


“እስራኤል ሆይ! ያንተ ጀግና በተራሮች ላይ ተገድሎ ወደቀ! ኀያላኑ እንዴት ወደቁ!


በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ አውድማ ለቅሶውን ባዩ ጊዜ “ይህ የግብጻውያን ለቅሶ እንዴት መሪር ነው?” አሉ። በዚህ ምክንያት በዮርዳኖስ ሜዳ ያለው የዚያ ቦታ ስም “አቤል ምጽራይም” ተባለ፤ ትርጒሙም በዕብራይስጥ “የግብጻውያን ለቅሶ” ማለት ነው።


ዳዊትም ለአበኔር ሐዘኑን በቅኔ ሲገልጥ እንዲህ አለ፦ “አበኔር እንደ ሞኝ ሰው ይሙትን?


ይህ የሚያወርዱት ሙሾ ነው፤ የሀገሪቱ ሴቶች ሙሾ ያሰማሉ፤ ለግብጽና ብዛት ላለው ሕዝብዋ ያወርዱታል፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።”


ያዘንኩትም ለወዳጅ ወይም ለወንድም የሚታዘነውን ያኽል ነው፤ እናቱ የሞተችበት ሰው የሚያዝነውን ያኽል ራሴን ዝቅ አድርጌ አለቀስኩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች