ከብታቸውንና ተክላቸውን ይባርክላቸው ነበር፤ በቤትና በምድረ በዳ የያዙትንም ሁሉ ይባርክላቸው ነበር፤ በዐይነ ምሕረት ይመለከታቸው ነበርና እንስሶቻቸውን አያሳንስባቸውም ነበር፤ የጻድቃን ልጆች ናቸውና ፈጽሞ ይወዳቸው ነበር።