በልቅሶና በኀዘን፥ በብዙ ልመናና በስግደትም ወደ ፈጠራቸው ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ የሚጨክኑም ብፁዓን ናቸው፤ ንስሓ የገቡትን ከሳታችሁ በኋላ ንስሓ የገባችሁ እናንተ የእኔ ናችሁ ብሏቸዋልና፤