በቀትርና በሰዓት በሥራው ሁሉ ይሰግድላቸውና ያመልካቸው ነበር፤ ይለምናቸውና ይተማመናቸውም ነበር፤ እንዲሁም ከመንገዱ በተመለሰ ጊዜ ይለምናቸው ነበር፤ የጣዖታቱ ካህናትም በነገሩት ሁሉ ፈቃዳቸውን ያደርግ ነበር።