ዳግመኛም የእስራኤል ልጆች የሚያደርጉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ያስተምሯቸው ዘንድ ወደ መኝታው የሚገቡ፥ ታናናሽ ቅምጥል ልጆቹን የሚጠብቁ ዐዋቂዎችን ከታናናሾቹ ሾመ፤ ሥርዐቱንና ሕጉን፥ አምልኮቱንና ፍርዱን፥ ሞዓባውያንም የሚያደርጉትን ሥርዐት ሁሉ ከምርኮ ልጆች ይሰማ ነበር።