እግዚአብሔርም በነቢዩ ቃል የተናገረውን መቅሠፍት እንደማያዘገይ ዐወቀ። ዐይኖቹ የተገለጡ ናቸውና አይተኛም፤ ዦሮውም የተከፈተ ነውና ቸል አይልም፤ የተናገረውንም ቃል ሐሰት አያደርግምና በአንዲት ጊዜ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ያደርጋታል።