የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በከ​ተ​ማ​ዋም በር አራት ለም​ጻ​ሞች ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እስ​ክ​ን​ሞት ድረስ በዚህ ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ የሚያሠቅቅ የቈዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች በከተማዪቱ መግቢያ በር አጠገብ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ በዚህ የምንቈየው ለምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቆያለን?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቈያለን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በበሩም መግቢያ አራት ለምጻም ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በርሳቸውም “እስክንሞት ድረስ በዚህ ለምን እንቀመጣለን?

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 7:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሶ​ርያ ንጉሥ ሠራ​ዊት አለቃ ንዕ​ማ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ እጅ ለሶ​ርያ ደኅ​ን​ነ​ትን ስለ ሰጠ፥ በጌ​ታው ዘንድ ታላ​ቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰው​ዬ​ውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለም​ጻም ነበረ።


ወደ ከተማ ብን​ገባ ራብ በከ​ተማ አለና፥ በዚያ እን​ሞ​ታ​ለን፤ በዚ​ህም ብን​ቀ​መጥ እን​ሞ​ታ​ለን። እን​ግ​ዲህ ኑ፥ ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር እን​ሂድ፤ በሕ​ይ​ወት ቢያ​ኖ​ሩን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ቢገ​ድ​ሉ​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ተባ​ባሉ።


ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የኤ​ል​ሳዕ ሎሌ ግያ​ዝን፥ “ኤል​ሳዕ ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ሁሉ ንገ​ረኝ” እያለ ይነ​ጋ​ገር ነበር።


ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ፥ አን​ተና ሕዝ​ብህ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለምን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ?


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ ተነሣ፤ እነ​ሆም፥ ማር​ያም ለም​ጻም ሆነች፤ እንደ በረ​ዶም ነጭ ሆነች፤ አሮ​ንም ማር​ያ​ምን ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ለም​ጻም ሆና ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው።