ዘኍል 12:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ እንደ በረዶም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፤ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሷት አየ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ደመናውም ከድንኳኑ በተነሣ ጊዜ እነሆ፥ ማርያም በለምጽ ደዌ ተይዛ እንደ በረዶ ነጭ ሆና ነበር፤ አሮንም ወደ ማርያም ዘወር አለ፥ እነሆም፥ በለምጽ ደዌ ተይዛ ተመለከተ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ፤ ጊዜ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ ለምጹም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፤ አሮን ወደ ማርያም በተመለከተ ጊዜ ለምጻም ሆና አያት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |